የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲ (ECUSTA) ከፍተኛ አስተዋጽዖ ካደረጉት ከወንድም አሚልካሬ ጋር በጽ/ቤታቸው ተገናኙ።

ነሐሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ከክርስቲያን ወንድሞች ማህበር አባል ከሆኑት ከክቡር ወንድም አሚልካሬ ጋር በጠቅላይ ጽ/ቤት ተገናኙ።

ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲ (ECUSTA) የልማት ሥራዎች፣ የመማሪያ ህንጻዎች፣ የላቦራቶሪ ክፍሎች እና ሌሎችንም ድጋፍ ማድረግ የሚችሉ አለም አቀፍ አጋር ተቋማትን በማስተባበር ከፍተኛ አተዋጽዖ ያበረከቱት ክቡር ወንድም አሚልካሬ በኢትዮጵያ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የክርስቲያን ወንድሞች ማህበር በኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት ዘርፍ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ ያለውን አስተዋጽዖ በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲን (ECUSTA) በማስተዳደር ለሚገኘው ይህ ማህበር አለም አቀፍ ማህበረሰቡን በማስተባበር ድጋፍ በማሰባሰብ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉትን ወንድም አሚልካሬን በቤተክርስቲያኗ ስም አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲ (ECUSTA) ፕሬዝደንት ወንድም ካሱ ፋንታዬ በበኩላቸው ወንድም አሚልካሬ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በጣልያን የጳጳሳት ጉባኤ መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠንከር የላቀ አስተዋጽዖ እንዳላቸው በመግለጽ አመስግነዋል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300