በሊዝበን ፖርቹጋል ላለፉት ቀናት በደማቅ ካቶሊካዊ ሥርዓት የተደረገው 37ኛው የአለም ወጣቶች ቀን
በሊዝበን ፖርቹጋል ላለፉት ቀናት በደማቅ ካቶሊካዊ ሥርዓት የተደረገው 37ኛው የአለም ወጣቶች ቀን
በሊዝበን ፖርቹጋል ላለፉት ቀናት በደማቅ ካቶሊካዊ ሥርዓት የተደረገው 37ኛው የአለም ወጣቶች ቀን ላለፉት ቀናት የተለያዩ የጸሎት መርሃግብሮች በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት ሲካሄዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ሀምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን በተገኙበት በመስዋዕተ ቅዳሴ ተጠናቋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ”ይህ ስብስብ ከኮቪድ ወረርሺኝ ከተከሰተ በኋላ በካቶሊካውያን ዘንድ የመጀመሪያው ትልቅ ስብስብ ነው” ያሉ ሲሆን ለዚህ መሳካት የተባበሩትን ሁሉ በተለይም አዘጋጅ ሀገሪቷን ፖርቹጋልን አመስግነዋል። አክለውም ለወጣቶች “አትፍሩ አይዟችሁ ኢየሱስ የእያንዳንዳችንን የሕይወታችንን ልብ ያውቃል፡ ሀዘናችንን፣ ስኬቶቻችንን እና ውድቀቶችንን ያውቃልና” ብለዋል። ርእሰ ሊቃነጳጳሳት በሰላም እጦት እና በተለያዮ ሀገራት ባሉ አለመረጋጋቶች ምክንያት በርካታ ወጣቶች በሊዝበን መገኘት ባለመቻላቸው ወጣቶች ለእነዚህ ወንድምና እህቶቻቸው እንዲሁም ስለመላው ዓለም ሰላም አበክረው እንዲጸልዩ እና የጥፋት ተልእኮ ተባባሪ ከመሆን ራሳቸውን እንዲያቅቡ አደራ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶችን በመወከል በ37ኛው የአለም ወጣቶች ቀን ለማክበር በሊዝበን ፖርቹጋል የተገኘው የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በተደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መባ አቅርበዋል።
በመርሃግብሩ ከአዲስ አበባ ሀገረስብከት የፊሶን የመዘምራን ቡድን የተገኙ ሲሆን በሊዝበን ከተገኙ በርካታ ወጣቶች ጋር የባህል እና የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከ10 ሀገረስብከቶች የተውጣጡ ወጣቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ በማስተባበር በዚህ ታላቅ መድረክ ቤተክርስቲያንን ለወከሉ ወጣቶች እና ይህንንም በማስተባበር ትልቅ ኃላፊነት የተወጣውን በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የወጣቶች ቢሮ እንዲሁም እያንዳንዱን መርሃግብር ከቦታው በምስል ሲያቀርቡ የነበሩትን የሠላም ካቶሊክ ቴሌቭዝንም ምስጋና እናቀርባለን።
በመጨረሻም 38ኛው የአለም ወጣቶች ቀን 2019 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ 2027) በደቡብ ኮሪያ እንደሚካሄድ ተገልጿል።