ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ የተላለፈ የኀዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጥቅምት አጋማሽ 2018 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ሚደግዱ አስተርዮ ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አካባቢ በተፈጸመው ግድያ የካቶሊካውያን ሕይወት ማለፉንና ንብረት መቃጠሉን በታላቅ ሀዘን ሰምተናል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  ምዕመናን ላይ ተመሳሳይ ግድያ መፈጸሙን ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ ሰምተናል።

ቤተክርስቲያናችን ይህን አይነቱን ኢ-ሰብዓዊ ተግባር አጥብቃ ታወግዛለች፤ በመሆኑም የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ መንግስት አስቀድሞ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች። 

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ  በዚህ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ዘለዓለማዊ እረፍትን ያገኙ ዘንድ እየጸለየች የተሰማንን ሀዘን ለመላው ካቶሊካውያን፣  ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ለተጎዱ ቤተሰቦች ፈጣሪ እውነተኛ መጽናናት እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን፡፡

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ  
ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን  
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት  

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300