የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ስኬታማ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች።


የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ በዘንድሮው ሀገር አቀፍ ፈተና በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ፣ ላሳያችሁት ብርታትና እና ጽናት ለቤተሰባችሁ፣ ለትምህርት ቤቶች እና ለቤተክርስቲያኒቱ ማህበረሰብ የኩራት ምንጭ ሆናችኋል።
በቅዱስ ዮሀንስ ደ ላ ሳል ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሲምቦ ደረጀ አያና 548 በሆነ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበች ሲሆን ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ሴት ተማሪዎች በማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች። እንዲሁም ተማሪ ዮርዳኖስ ዘውዴ በነቀምቴ ኪዳነምህረት ካቶሊክ ትምህርት ቤት በተፈጥሮ ሳይንስ 559 በማምጣት ክፍተኛ ነጥብ አስመዝግቧል። የእነሱ ስኬት የሁላችንም ስኬት ነዉ በተለይም የመምህራኖቻቸው የወላጆች ጥረት ሊመሰገን ይገባል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከ120 ዓመታት በላይ በዘመናዊ ትምህርት ፈር ቀዳጅ ሆና ዛሬ በመላ ሀገሪቱ በ545 ትምህርት ቤቶች እና በ1 ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ ዜጎች ጥራት ያለዉ ትምህርት በመስጠት ላይ ትገኛለች። ቤተክርስቲያን እውቀትን ከስነ ምግባር ጋር አጣምራ በመስጠት የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ማፍራቷን ትቀጥላለች።
