የኢትዮጵያ ወጣት ካቶሊካውያን የበጎ ፍቃደኞች ፕሮግራም በሆሳዕና እና በሶዶ ሀገረስብከት

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ብሔራዊ የወጣቶች ቢሮ ከቅርብ ምስራቅ ካቶሊክ የበጎአድራጎት ማህበር በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ወጣት ካቶሊካውያን የበጎ ፍቃደኞች ፕሮግራም በሆሳዕና እና በሶዶ   ሀገረስብከት አስጀመረ። 

በወጣቶች ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ በማተኮር የሚሰራው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ብሔራዊ የወጣቶች ቢሮ በጎ ፍቃደኛ ካቶሊክ ወጣቶች ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት በአዲግራት ሀገረስብከት ይፋ ያደረገ ሲሆን ፕሮጀክቱ አምስት ሀገረስብከቶችን በማሳተፍ በብሔራዊ ጽ/ቤት አሰተባባሪነት ተጀምሯል። 

በሆሳዕና ሀገረስብከት በተካሄደው ስልጠና  የሰበካው ሀዋሪያዊ ቢሮ  አስተባባሪ የሆኑት ክቡር አባ አዳነ ወልደ ማሪያም እንዲሁም የልማት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ ክቡር አባ አማኑኤል ዮሴፍ ተገኝተው ወጣቶችን ለዚህ ፕሮግራም እድል በማግኘታቸው በማበረታታት ክቡር አባ አዳነ  የመክፈቻ ጽሎት እና የመክፈቻ ነግግር አድርገዋል። እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆነችው ወ/ሪት የምስራች  አሰፋ ስለ ፕሮግራሙ ሂደት በዝርዝር ገልጻለች። 

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ “የቅድስና ጥሪ” ሐዋርያዊ ማነቃቂያ በአባ አማኑኤል  ዮሴፍ ለመንፈሳዊ ማነቃቂያ እና ማበረታቻ እንዲሆን  በዚህ ዘመን ቅድስና የሚቻል መሆኑን የሚያረጋግጥ ይዘት ያለውን ሰነድ  ለወጣቶች  አስተምረዋል። 

ከዚያም በመቀጠል ወጣቶች  ለስራ ላይ ልምምድ ይረዳቸዋል ተበሎ የሚታሰበውን  የክህሎት ስልጠና ሲወስዱ ቆይተዋል። በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ የሆሳዕና ሀገረስብከት የልማት ክፍል ሰራተኛ የሆኑት አቶ ቢኒያም በሥልጠናው በመገኘት ወጣቶች የተመደቡባቸውን እና የሚሰሩባቸውን የስራ ቦታዎች በማሳወቅ በሆሳዕና ሀገረስብከት በሚኖራቸው የበጎፈቃድ ቆይታ ላይ ሁሉ ለመተባበር ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ ስልጠናው በሶዶ ሀገረስብከት በተካሄደው ስልጠና ብፁዕ አቡነ ደጀኔ የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ ወጣቶችን አበረታተው ፕሮግራሙን አስጀምረዋል።  

የስልጠናው አካል የሆነው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ “የቅድስና ጥሪ” ሐዋርያዊ ማነቃቂያ የካፑቹን ማህበር አባል በሆኑት ክቡር አባ ወርቁ ደመቀ በቦታው ተገኘተው ለወጣቶቹ በመልዕክቱ ላይ ወጣቶች ስራቸውን እንደ ቅድስና መንገድ በማየት መጓዝ እንዲችሉ ማድረግ ያሉባቸውን መሰረታዊ ዝግጅቶችን አስተምረዋል። 

በመዝጊያውም ብፁዕ አቡነ ደጀኔ ተገኝተው ሰልጠናውን በመጨረሳቸው የመልካም ምኞት መልክታቸውን አስተላልፈው ወደፊት ለሚጠብቃቸው ሀላፊነት እንዲዘጋጁ እና የተሰጣቸውን እድልም በአግባቡ እንዲጠቀሙ አበረታተው ስልጠናው ተጠናቋል። 

ፕሮጀክቱ በተለያዩ ሰበካዎች የሚገኙ ወጣቶች በከፍተኛ ትምህርት ተመርቀው የሥራ ዕድል እስከሚያገኙ ባለበት ወቅት የአቅም ግንባታ፣ እና የክህሎት ስልጠና በማመቻቸት ወጣቶች የሥራውን አለም በተሻለ ዝግጅት እንዲቀላቀሉ የሚያግዝ እና የሚያመቻች መሆኑን ተገልጿል። 

ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የተባበሩትን የሆሳዕና እና የሶዶ ሀገረስብከት ሀዋሪያዊ እና ማህበራዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች፣ የቅርብ ምስራቅ ካቶሊክ የበጎ አድራጎት ማህበር በኢትዮጵያ እንዲሁም የቅዱስ ዮሀንስ ዳግማዊ ኮሌጅን በማመስገን መርሃ ግብሩን አጠናቀዋል። 

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300