20ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ እሑድ ሐምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ማካፓ ስታዲየም በታላቅ ድምቀት በይፋ ተከፍቷል።
20ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ እሑድ ሐምሌ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ማካፓ ስታዲየም በታላቅ ድምቀት በይፋ ተከፍቷል።
የመክፈቻ ስነስርዓቱ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 2 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ከመላው ታንዛኒያ የተወከሉ እና የተሰባሰቡ ካቶሊካውያን ህጻናት፤ ወጣቶች፤ እናቶች እና አባቶች በደማቅ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነስርዓት ለአመሲያ አባል ሀገራት ብጹዓን ጳጳሳት፣ ካህናት ደናግላን እና ከተለያዩ ማህበራት እና የሥራ ዘርፍ ለተወከሉ ምዕመናን አቀባበል አድርገዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤም በብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የተመራ ልዑካን ብጹዓን ጳጳሳት፣ ካህናት እና ምዕመናን በመያዝ በዕለቱ በመክፈቻው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ተገኝተዋል።
መስዋዕተ ቅዳሴው ከሁሉም አባል ሀገራት በተወከሉ ብጹዓን ጳጳሳት የተመራ ሲሆን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልዕከት፤ የ20ኛው ጉባኤ መሪ ቃል “የሁላችንም መኖሪያ ቤት የሆነችውን ምድርን እንንከባከብ” መሰረት በማድረግ የተላለፈ መልዕክት እንዲሁም የእንኳን ደህና መልዕክቶች ተላልፈዋል።