58ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ 58ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን ሞጆ በሚገኘው የኮንሶላታ ልዑካን የሱባኤ ማዕከል ሀምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምረዋል።

ብፁዓን ጳጳሳት በጉባኤው አጀንዳቸው የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ላይ በማተኮር ሐዋርያዊ እና ማህበራዊ ልማት አገልግሎቶች፣ ወቅታዊ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እና ሌሎችም የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በመመወያየት አቀጣጫ እና መመሪያዎችን እንደሚሰጡ የጉባኤው ጠቅላይ ጸኃፊ ክቡር አባ ከተማ አስፋው ገልጸዋል።

ጉባኤው በቀጣይ ቀናት እስከ ሀምሌ 4 ቀን የሚቆይ ሲሆን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300