59ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ።



የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ 59ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን በእምድብር ሀገረስብከት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምረዋል።

ጉባኤው የ12 ሀገረስብከት ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በብፁዕ ሊቀጳጳስ ብሪያን የቅድስት መንበር ተወካይ በተገኙበት ተጀምሯል። በጉባኤው ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲግራት ሀገረስብከት ጳጳስ በወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት አለመገኘታቸው ተገልጿል።

ጉባኤው በአጀንዳው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በርካታ ጉዳዮችን እንደሚዳስስ የተገለጠ ሲሆን በተለይም የሲኖዶስን የመጨረሻ ሰነድ በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችሉ አቅጣዎችን እንደሚያስቀምጥ የጉባኤው የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ገልጸዋል።
ጉባኤው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዮ 14ኛ መልዕክት በማዳመጥ የተጀመረ ሲሆን ይህም ጉባኤው ከቅድስት መንበር ጋር ያለውን ህብረት የሚያመላክት ነው።
ጉባኤው በቀጣይ ቀናት እስከ ታህሳስ 2 ቀን የሚቆይ ሲሆን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300