ክርስቶስ ሕያው ነው
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የወጣቶች ቢሮ አስተባባሪነት ወደ አማርኛ ተተርጉሞ የተዘጋጀው “ክርስቶስ ሕያው ነው” የተሰኘው መጽሐፍ በብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ተባርኮ ለአገልግሎት ተሰራጭቷል።
“ክርስቶስ ሕያው ነው” የተሰኘው ሰነድ እ.አ.አ. በ2018 ከተከናወነው የወጣቶች ሲኖዶስ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተለይ ለወጣቶች የተላለፈ ሐዋርያዊ መልዕክት ነው።
ይኸው በላቲን ቋንቋ “CHRISTUS VIVIT” በሚል ለወጣቶች የተላለፈው ሐዋርያዊ መልዕክት በክቡር አባ ዳንኤል አሰፋ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ቀርቧል።
ወጣት ቢሮውም ይህንን መፅሐፍ ለወጣቶች የአዲስ አመት ገፀ በረከት ይሆን ዘንድ አበርክቷል። ወጣቶች አንብበው እንዲባረኩበትም ግብዣውን ያቀርባል።
መልካም አዲስ አመት!
.