20ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. የመክፈቻ ስብሰባዉን አድርጓል።
20ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. የመክፈቻ ስብሰባዉን አድርጓል።
20ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በዛሬው እለት የመክፈቻ ስብሰባዉን በጁሊየስ ኔሬሬ አለምአቀፍ የስብሰባ አዳራሽ 150 ጳጳሳት፤ በርካታ ካህናት እና ደናግላን፤ የአለም አቀፍ የአጋር ድርጅት ተወካዮች፤ የአባል ሃገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጀምሯል።
በዛሬው ዕለት በነበራቸው ቆይታ ብጹዕ አቡነ ቻርለስ ካሶንዴ የአመሲያ ሊቀመንበር ለተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። 20ኛው የጳጳሳት ጉባኤ መሪ ቃል “ተፈጥሮን መንከባከብ በሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያለው ተጽዕኖ” የብፁዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል ርእስ የተላለፈውን ሐዋርያዊ መልዕክት መሰረት በማድረግ የተመረጠ መሆኑን ገልጸዋል። ብጹዕ አቡነ ቻርለስ ካሶንዴ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ምድርን የመንከባከብ ኃላፊነት በተግባር ላይ ለማዋል ሁሉም የተጠራ ሲሆን በተለይም ካቶሊካውያን ከሌሎች ሀይማኖት አባላት ጋር በመሆን የጋራ ምድርን የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለብን አሳስበዋል። በመቀጠልም ብጹዕ ካርዲናል ታግሌ የጉባኤውን ዋና መልዕክት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሀሳብ በመነሳት አስተላልፈዋል።
የአመሲያ አመሰራረት፤ ታሪክ እና በአገልግሎት የገጠሙ ተግዳሮቶች እና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማቅረብ የዘንድሮውን የ20ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መሪ ቃል እና አርማ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የቤተክርስቲያን አጋር ድርጅቶች የአብሮነት መልዕክቶች በተገኙት ተወካዮች ተላልፈው የዕለቱ መርሃግብር ተጠናቋል።