የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የትምህርት ተቋማት አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ብፁዓን ጳጳሳት፣ የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን ተወካዮች፣ የኢሮሚያ ክልል የትምህርት ቢሮ ተወካዮች፣ የሀገረስብከት የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና የጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የትምህርት ተቋማት አመታዊ ጉባኤ ተካሂዷል።
በጉባኤው ያሳለፍነው ዓመት የትምህርት ዘርፍ አፈጻጸም፣ አዲሱ የትምህርት አዋጅ ዝርዝር እና ተግባራዊነት፣ እና ሌሎችም የዘርፉ ጉዳዮች ተቃኝተዋል።
ፎረሙ የመንግስት ተወካዮችን ለፓናል ውይይት የጋበዘ ሲሆን ከትምህርት አዋጅ ጋር ተያይዞ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምክረ ሀሳብ፣ የመፍትሔ አቅጣጫዎች እና በመንግስት በኩል የትብብር አማራጮችን አመላክተዋል።
ጉባኤው አዲስ የወጣው የትምህርት አዋጅን ከቤተክርስቲያኗ የትምህርት ተቋማት ህጋዊ ምዝገባ አኳያ በጥልቀት ተወያይቷል፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በትምህርት አገልግሎት ዘርፏ ከ180 ዓመት በላይ ያስቆጠረች ሲሆን በአመት ከ200ሺህ በላይ ተማሪዎችን በ545 የትምህርት ተቋማት መድረስ ችላለች።

