የጳጳሳዊ ልዑካን ማህበር በኢትዮጵያ ለ2018 ዓ.ም. የወንጌል ተልዕኮ ቀን ምዕመናን እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀረበ።

የጳጳሳዊ ልዑካን ማኅበራት በኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ለሚከበረው የተልዕኮ ቀን በሀገራችን ጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚከበር በመሆኑ ምዕመናን በልግስና እንዲያከብሩ አሳውቋል።

“ከሁሉም ህዝቦች መካከል የተስፋ ሚስዮናውያን(ልኡካን) ስለመሆን!”

በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው የተልዕኮ ቀን የተጠመቁትን ሕዝቦችና መላውን ቤተክርስቲያንን በተለያየ ሥራ መስክ ተሰማርተው የሚያገለግሉት አገልጋዮች በሙሉ በክርስቶስ ፈለግ የመልካም ምሥራችና ተስፋ መልእክተኞች በመሆን የተስፋ ፈጣሪዎች እንድንሆን ጥሪ ቀርቦልናል።

የልዑካን ማህበሩ ዋና አላማቸው ስብከተወንጌል ማዕከል በማድረግ ህዝብ እግዚአብሐርን በካቶሊክ ቤተክርስስቲያን የወንጌል አብሳሪ ይሆኑ ዘንድ መቀስቀስ፣ ማሳተፍና እና ማበረታታት ሲሆን እነዚህም የልዑካን ማህበራት ምዕመናን ካሉበት በተለያየ መልኩ ወደ ሌሎች ለመድረስ የሚችሉበትን፣ጠንክረው በስብከተ ወንጌል ሥራ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ድልድይ ሆነው ያገለግላሉ፡፡

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300