የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚፈጸሙ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን አወገዙ።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የሚፈጸሙ ኢሰብዓዊ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአርሲ ዞን በተደጋጋሚ በበርካታ ንፁኃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ድርጊቶችን አጥብቀው አውገዘዋል።

ብፁዕነታቸው “ቤተክርስቲያናችን ይህን አይነቱን ኢሰብዓዊ ተግባር አጥብቃ ታወግዛለች በመሆኑም የዜችን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ መንግስት አስቀድሞ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ኃላፊቱን እንዲወጣ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች። ”ብለዋል።

አክለውም “ይህ  ሆን  ብሎ  የንጹሕንን  ሕይወት  ማጥፋት  በእግዚአብሔር  ፊት  ከባድ  ኃጢአት እና በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠረ ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጠውን ቅዱስ ክብር መጣስ ነው” ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል መከላከያ በሌላቸው ንፁኃን የሚፈፀም ማንኛውም አይነት ጥቃት በሃይማኖት፣ በጎሳ ወይም በፖለቲካዊ ጥቅም ሊስተባበል የማይችል መሆኑን ገልጸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥላቻን እንዲቃወሙና እንዲህ ያሉ አሳዛኝ ክስተቶችን በመጠቀም በማህበረሰባችን መካከል ክፍፍል ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎችን እንዲያወግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ካቶሊክ ከመላው የኃይማኖት ተቋማት እና በጎ ፍቃድ ካላቸው ሰዎች ሁሉ ጋር በመተባበር  በንጹኃን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ዓይነት ጥቃት እንደምታወግዝ ተገልጿል።

ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸው መጨረሻ ለተጎዱ ቤተሰቦች መጽናናትን፣ እና ለኢትዮጵያ ሃገራችን እንዲሁም ለመላው አለም ሰላምን እንዲያወርድ ፈጣሪን ተማጽነዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤም በዚህ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ዘለዓለማዊ እረፍትን ያገኙ ዘንድ በመጸለይ የተሰማውን ታላቅ ሀዘን ይገልጻል።


Leave a Reply

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300