ከኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን የጤና ሁኔታ አስመልክቶ የቀረበ የጸሎት ጥሪ

“ጌታ በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።” — መዝሙር 41፥3

       የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ፤ በሀገራችን በሚገኙ ካህናት፣ ገዳማውያን እና ገዳማውያት፣ ካቶሊካውያን ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸውን ወገኖች ሁሉ በመወከል ከኩላዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር በአንድነት ቅዱስነታቸው ሌዎ 14ኛ ከህመማቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ ጸሎቱን ያቀርባል።

        የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን  የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሕመም እና የቀዶ ጥገና ሕክምና ዜና ከሰማንበት ዕለት አንስቶ፣ በጸሎታችን በማሰብ ቅዱስነታቸው ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ጥበቃ ሥር በጸሎት እያቀረብናቸው እንገኛለን።

        ቅዱስነታቸው ቀዶ ጥገናቸውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቀው፣ ከህመማቸው በማገገም ላይ በመሆናቸው ልባችን በታላቅ ደስታና ምስጋና ተሞልቷል።

        የሁሉ አባት የሆነው አምላካችን እጁን ዘርግቶ በቅዱስነታቸው ላይ የጀመረውን ጥበቃና ፈውስ እንዲያጸናላቸው፣ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በብቃትና በጥንካሬ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሙሉ ጤናንና ጽኑ ብርታት ይሰጣቸው ዘንድ በአንድነትና በትጋት ሁላችንም በጸሎት እንድንበረታ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

        የቤተክርስቲያን እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስነታቸውን በእናትነት ጥበቃዋ እንድታማልዳቸው እንለምናለን።

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር፣

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ


Leave a Reply

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300