በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት የአሪዮ (ጥበብ) የትምህርት ተቋም ተመረቀ።

በእየሱሳውያን የአባቶች ገዳም አማካይነት የተገነባው የአሪዮ (ጥበብ) የትምህርት ተቋም በቦንጋ ከተማ የተገነባ ሲሆን ለአካባቢው ልጆች የትምህርት ህልምን የሚያሳካ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።

ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም የተመረቀው ይህ ተቋም በውስጡ በርካታ የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ክፍሎች፣ ትምህርት ቤቱ የካቶሊክ ኢየሱሳዊያን ማህበር የተገነባ ሲሆን የኮምፒውተር፣የኬሚስትሪ፣ የባዮሎጂ እና የፊዚክስ በተ ሙከራዎችን ያከተተ መሆኑ ተገልጿል።

ተቋሙ ከኢትዮጵያም ባሻገር በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ያለውን መስፈርት በማሟላት መገንባቱን የገለጹት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ክቡር አባ ጴጥሮስ ኦሞዲ በአሁኑ ወቅት 40 ተማሪዎችን በመመዝገብ አገልግሎት መጀመሩን ገልጸዋል።

በመርሃግብሩ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት ጳጳስን በመወከል ክቡር አባ ከተማ አስፋው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ፣ ክቡር አባ ሳሙኤል የጅማ ቦንጋ ሀገርስብከት እንደራሴ፣ ዶክተር ተክለ አቡሎ የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ክቡር አባ ከተማ አስፋው ተቋሙን ያስገነባውን የእየሱሳውያን የአባቶች ገዳምን በማመስገን ከትምህርት ተቋም በላይ የከፋ ምድር ታሪካዊ ቅርስ እንደሚሆን ገልጸዋል። በዚህ ግንባታ ሂደት የተሳተፉ ተባባሪ በጎ አድራጊ እና የመንግስት አካላትንም አመስግነዋል።


Leave a Reply

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300