ክቡር አባ አብርሃም ገብረማርያም በኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላላ ጽ/ቤት የሐዋርያዊ ስራዎች ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአገልግሎት ዘርፍ የሆነው የሐዋርያዊ ስራዎች ሲሆን ይህን ዘርፍ በጠቅላይ ጽ/ቤት ደረጃ በኃላፊነት እንዲያገለግሉ ብፁዓን ጳጳሳት የሆሳዕና ሀገረስብከት ካህን የሆኑትን ክቡር አባ አብርሃም ገብረማርያምን ሾመዋል።

ክቡር አባ አብርሃም በሆሳዕና ቀጨቢራ ወረዳ ሌሙቴ መንደር እ.ኤ.አ. 1971 የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተወለዱበት አካባቢ በመጨረስ ለክህነት ትምህርት ራሳቸውን ዝግጁ አድርገዋል። የዘርዓ ክህነት ትምህርታቸውን ዝግጅት በቅድሚያ በሆሳዕና ለሁለት ዓመት ቆይታ አድርገው ወደ በአዲስ አበባ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት የነገረ መለኮት እና የፍልስፍና ትህምርታቸውን ጨርሰው እ.ኤ.አ. በ2003 የምስጢረ ክህነት ዝግጀታቸውን አጠናቅቀዋል። በመቀጠልም ሮም በሚገኘው ኡርባኒያና ጳጳሳዊ ዩኒቨርስቲ የነገረ መለኮት ትምህርት በዲግሪ መርሀግብር ትምህርታቸውን ያገኙ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በዲፕሎማ ፕሮግራም በአልፋ ዪኒቨርስቲ ኮሌጅ የህግ ትምህርት አጥንተዋል።

ክቡር አባ አብርሃም የመጀመሪያ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን እ.ኤ.አ. 2002 ዓ.ም. ጀምሮ ከድቁና እስከ ቆሞስ ከዚያም የትመህርት ቤት ኃላፊ በመሆን ለበርካታ አመታት በተለያዩ ቁምስናዎች እና ትምህርት ቤቶች አገልግለዋል። ከሁለት አስርት አመታት በላይ በነዚህ ሃላፊነቶች ቆይታ ካደረጉ በኋላ ከእ.ኤ.አ. 2023 ጀምሮ በጠቅላይ ጽ/ቤት የአለም አቀፍ የጳጳሳዊ ልዑካን በኢትዮጵያ ኃላፊ እንዲሁም በሆሳዕና ሀገረስብከት የሐዋርያዊ ሥራዎች አስተባባሪ በመሆን በጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሐዋርያዊ ሥራዎች ኃላፊነት እስከተሾሙበት ወቅት ድረስ በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ጽ/ቤታችን ክቡር አባ አብርሃም በኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት በሚኖራቸው የአገልግሎት ዘመን መልካሙን ሁሉ እየተመኘን እንኳን ደህና መጡ ለማለት ይወዳል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300