ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ የብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለቅድስት መንበር ያቀረቡትን ከኃላፊነት የመነሳት ጥያቄ ተቀበሉ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ እና የአዲስ አበባ ሀገረሰብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ በጡረታ ምክንያት ሐዋርያዊ ኃላፊነታቸውን አሰረከቡ።
ለቅድስት መንበር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በዛሬው ዕለት ጥያቄያቸውን መቀበላቸውን በቅድስት መንበር ልዪ መልዕክተኛ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ አማካይነት ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ተደርጓል።
የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ተተኪ በመሆን የአዲስ አበባ ረዳት ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ሆነው ተሹመዋል።

