የሀዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮር አረርቲ ደበረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የተሠራ የእንጨት ርብራብ በመደርመሱ ምክንያት ለደረሰው አስድንጋጭ አደጋ ሀዘኑን ገለጸ።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና ለሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በላኩት የሀዘን መግለጫ ለአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ እና ለተጎዱ ቤተሰቦች ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝተዋል።

ጌታ ሆይ ለሞቱት ሰዎች
የዘላለም እረፍት ስጣቸው
የዘላለም ብርሃን አብራላቸው
በሰላም አሳርፋቸው!

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300