የቅዱስ ፍራንቼስኮስ ቅሪተ አካል ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።

የሰላም መሳሪያ፣ የተፈጥሮ ባልደረባ የሆነው የቅዱስ ፍራንቼስኮስ ቅሪተ አካል ወደ ኢትዮጵያ መጣ።
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቅዱስ ፍራንቼስኮስ ታናናሽ ወንድሞች ቅሪተ አካሉን ከጣልያን ወደ ኢትዮጵያ ለምዕመናን በረከት ይሆን ዘንድ እንዲመጣ አድርገዋል።
ቅሪተ አካሉም አመታዊ በቅዱስ ፍራንቼስኮስ ክብረ በዓል ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ለህዝብ ይፋ ሆኗል።
የቁምስናው ቆሞስ ክቡር አባ ፍስሃ ታፈሰ እንደገለፁት የቅዱስ ፍራንቼስኮስ ቅሪተ አካል በቁምስናው በቋሚነት የሚቀመጥ ሲሆን መላው ምዕመናን በዚህ በመገኘት በቅዱሱ አማላጅነት ጸሎታቸውን ወደፈጣሪ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ቅዱስ ፍራንቼስኮስ በድህነት እግዚአብሔርን በእምነት እና በስራ በመኖር ለበርካቶች የቅድስና መንገደን ያሳየ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ቅዱስ ነው።
ቅዱስ ፍራንቼስኮስ ምዕመናን እና በጎ ፍቃድ ላለቸው ሰዎች ሁሉ በትህትና፣ በድህነት፣ተፈጥሮን በመንከባከብ፣ የሰላም መሳሪያ በመሆን፣ በንስሃ እና ዘወትር ወደቅዱስ ቁርባን በመቅርብ ለፈጣሪ ቅርብ እንዲሆኑ ያገዘ ቀዱስ ነው።
