“ለሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን በኅብረት፣ ተሳትፎ፣ ተልእኮ” የሲኖዶስ የመጨረሻው ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ።

በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሐዋርያዊ ስራዎች ጽ/ቤት አስተባበባሪነት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ሲኖዶስ ዐሥራ ስድስተኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውጤት የሆነውን “ለሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን በኅብረት፣ ተሳትፎ፣ ተልእኮ” የመጨረሻው ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀርቧል።

ከህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሞጆ የኮንሰላታ አባቶች ገዳም በመካሄድ ላይ ባለው አውደጥናት በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት የተካሂደውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሲኖዶስ የመጨረሻው ጉባኤ ውጤት በአማርኛ ተተርጉሞ ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ረዳት ጳጳስ እና በርካታ የቤተክርስቲያን ተወካዮች በተገኙበት ተባርኳል።

በአውደጥናቱ የሁሉም ሀገረስብከት የጳጳሳት እንደራሴዎች፣ የሐዋርያዊ ሥራ አስተባባሪዎች፣ የልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የጠቅላይ ጽ/ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የምዕመናን፣ የካታኪስት እና የወጣት ተወካዮች ተገኝተዋል።

መርሃግብሩ በመስዋዕተ ቅዳሴ የተጀመረ ሲሆን የሲኖዶስ ሰነድ ምርቃት፣ የምዕመናን የስብከተ ወንጌል ሚና እና የሲኖዶስ ሰነድ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ዋና ዋና አጀንዳዎች በማድረድ ለቀጣይ አራት ቀናት እንደሚቆይ የሐዋርያዊ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ክቡር አባ አብርሃም ገብረማሪያም ገልጸዋል። በተጨማሪም የሐዋርያዊ እና የልማት ጽ/ቤቶች የጋራ ጉባኤ የሚደረግ ሲሆን ጽህፈት ቤቶቹ በጋራ መስራት የሚችሉበት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በአውደጥናቱ ማጠቃለያም ይህን የሲኖዶስ ሰነድ በተግባር ላይ እንዲውል አቅጣጫ በማስቀመጥ እና ሁሉን ያቀፈ አፈጻጸም እንዲኖረው በማደረግ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በሲኖዶስ ሂደት ውስጥ በቁምስና፣ በሀገረስብከት፣ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና፣ በአህጉር አቀፍ እና በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተሳትፋለች።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300