የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢዮቤልዩ ቅዱስ አመት የመዝጊያ መስዋዕተ ቅዳሴ ተካሄደ።

የኢዮቤልዩ ቅዱስ አመት የመዝጊያ መስዋዕተ ቅዳሴ በእምድብር ሀገረስብከት ቅዱስ አንጦኒዮስ ካቴድራል ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ተካሄደ። የስምንት ሀገረስብከት ብፁዓን ጳጳሳት በመስዋዕተ ቅዳሴው የተገኙ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ መስዋዕተ ቅዳሴውን አሳርገዋል።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ለቅዱስ አመት መዝጊያ ባስተላለፉት መልዕክት የኢዮቤልዩ አመት የቅድስት መንበር ይፋዊ መክፈቻ መርሃብሮችን አስታውሰው በ2025 ታይቶ በማይታወቅ የምሕረት ምልክት በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በሮም ሬቢቢያ ማረሚያ ቤት ቤተ ጸሎት ልዩ የሆነ የቅዱስ በር መክፈታቸውን ገልጸው ይህም የኢዮቤልዩን በረከት ለሁሉም የኅብረተሰብ አካል ማስፋት የቻለ ታላቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ለቅዱስ አመት መዝጊያ ባስተላለፉት መልዕክት የኢዮቤልዩ አመት የቅድስት መንበር ይፋዊ መክፈቻ መርሃብሮችን አስታውሰው በ2025 ታይቶ በማይታወቅ የምሕረት ምልክት፣ በሬቢቢያ እስር ቤት ጸሎት ቤት ውስጥ ልዩ የሆነ የቅዱስ በር በቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ መሆኑን ገልጸው ይህም የኢዮቤልዩን በረከት ለሁሉም የኅብረተሰብ አካል ማስፋት የቻለ ታላቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው “ይህ ቅዱስ አመት በተለይም ሀገራችን በተጨነቀችበት፣ የብዙኃን ህይወት በሚቀጠፍበት በዚህ እጅግ አስጨናቂ ወቅት በጌታችን መድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተስፋ አድርገን እዚህ ስላደረሰን ፈጣሪን ልናመሰግን ይገባል” ብለዋል።
በተያያዘም እ.ኤ.አ በ2025 ቅዱስ አመት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በዓልን በላቲን ሥርዓትም ሆነ በምስራቅ ካቶሊክ እና በምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በተመሳሳይ ቀን መከበር፤ ሀገራችን አራት አዳዲስ ጳጳሳትን ያገኘችበት ዓመት መሆኑ፤ ለ3 ዓመታት ውይይት ስታደርግበት የቆየውን የሲኖዶስ ሂደት ያጠናቀቀችበት እና የመጨረሻውን ሰነድ ይፋ ያደረገችበት ዓመት፤ መላው አለምን ያስደነገጠው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ህልፈተ ህይወት፣ ቀጥሎም ግን በተስፋ የጠበቅነው አምላክ ሳያሳፍረን አዲስ እረኛ የሆኑንን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የሰጠን ዓመት፤ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበት ዓመት መሁኑን አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሰበካዎች በዛሬው ዕለት ካቴድራል ውስጥ ያሉትን ቅዱስ በሮች የሚዘጉ ሲሆን በቅድስት መንበር እ.ኤ.አ ጥር 6 ቀን 2026 የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት የሚዘጋ ይሆናል።
