የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የማህበራዊ ልማት ጽ/ቤት 26ኛ ልዩ ጉባኤውን አካሄደ።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የማህበራዊ ልማት ጽ/ቤት ልዩ ጉባኤውን አካሄደ። ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ብፁዓን ጳጳሳት፣ የቦርድ አባላት፣ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተወካዮች በተገኙበት በጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት አካሄደ።

በጉባኤው የልማት ጽ/ቤቱ የተተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ  የቀረበ ሲሆን ሀምሌ 2011 ዓ.ም. የጸደቀው ድንብ ላይ ቤተክርስቲያኗ አስፈላጊነታቸውን ያመነችባቸው አንቀጾች ላይ ማሻሻያዎች ተደርጎ መቅረቡ ተገልጿል።

የተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ 47 አንቀጾችን የያዘ ሲሆን የስያሜ እና የአርማ ለውጦችን ያካተተ ሲሆን በቀጣይም በተግባር ላይ ለማዋል ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።

በተጨማሪም በጉባኤው የቀድሞ የልማት ጽ/ቤቱ የቦርድ ፕሬዝደንት የነበሩትን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመቂ ሀገረስብከት ጳጳስ ለነበራቸው ቆይታ በማመስገን በ59ኛው የጳጳሳት ጉባኤ ለኮሚሽኑ መሪነት የተሾሙትን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መርሃክርስቶስን ተቀብሏል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300