የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጤና ተቋማት አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት ከ25 ሚሊዮን ሰዎች በላይ የጤና አገልግሎት በ89 የጤና ተቋማት በመስጠት ላይ የምትገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. አመታዊ የጤና ተቋማት ጉባኤ አካሄደች።

በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ብፁዓን ጳጳሳት፣ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የሀገረስብከት የጤና ክፍል ኃላፊዎች እና የጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጤና ተቋማት አመታዊ ጉባኤ ተካሂዷል።


“በርኅራኄ፣ በፍቅር እንክብካቤ እናገለግላለን” በሚል መሪ ቃል በርካታ የጤና አገልግሎቶችን የምሰጠው ቤተክርስቲያኗ በዓመት ከ5 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ትደርሳለች። በተቋማቱ ከሚሰጡት ህክምናዎች በዋነኝነት የወባ፣ የሳምባ ነቀርሳ፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምና እና ቅድመ ጥንቃቄ ግንዛቤ ተሰጣለች። ከእነዚህም በተጨማሪ ለታካሚዎች የማማከር አገልገሎት እንዲሁም የህክምናውን ዘርፍ አስተዳደር ለማጠንከር እና ለማዘመን በአስተዳደር ላይ ለሚሰሩ ሥልጠናዎችን በመስጠት በትኩረት ትሰራለች።

በጉባኤው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የጤና ክፍል በሀገር አቀፍ እና በሰበካ ደረጃ ያከናወናቸውን ተግባራት የተገለጹ ሲሆን በተጨማሪም ከተለያዩ ሀገረስብከቶች የተወከሉ የጤና ተቋማት ልምዶቻቸውን አካፍለዋል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300