የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲ (ኢኩስታ) ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እ.ኤ.አ ለ2025 ያዘጃጋቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

ዩኒቨርስቲው 33 የህክምና ሳይንስ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን በተጨማሪም በላቦራቶሪ ቴክኒሺያን፣ እና በማህበራዊ አገልግሎት በአጠቃላይ 55 ተማሪዎችን ለቡ በሚገኘው ዋና ካምፓስ ጥር 2 ቀን 2018ዓ.ም. አስመርቋል።

በዚህ ታሪካዊ የምርቃት ሥነሥርዓት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የዪኒቨርስቲው ቻንስለር፣ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ሲልቫኖ ቶማዚ የቀድሞ የቫቲካን አምባሳደር በኢትዮጵያ እና ሞንሲኞር ማሲሞ ካቴሪኒ የቅድስት መንበር ተወካይ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የጅማ ቦንጋ ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ስዩም የሆሳዕና ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የእምድብር ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ደጀኔ የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ፣ ክቡር ወንድም ካርሎስ የደ ላ ሳል የወንድሞች ገዳም እንደራሴ፣ ክቡር አባ ከተማ አስፋው የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽኃፊ እና የዩኒቨርስቲው ቦርድ ሊቀመንበር፣ እና ክቡር ወንድም ካሱ ፋንታዬ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ተገኝተዋል።


የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲ (ኢኩስታ) ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ተቋቁሞ የደ ላ ሳል ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር አባል በመሆን በላሳሊያን የወንድሞች ገዳም የሚመራ ሲሆን “አዕምሮን ማስተማር፣ ልብን መንካት እና ህይወትን መቀየር” በሚል መሪ ቃል በርካታ በቴክኒካል ዕውቀት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት የሚችሉ ዜጎችን በማፍራት ላይ ይገኛል።
በዕለቱም የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርስቲ መድኃኔዓለም (ምህረተ አምላክ) ቤተክርስቲያን ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና ብፁዕ ካርዲናል ሲልቫኖ ቶማዚ የቀድሞ በኢትዮጵያ የቫቲካን አምባሳደር በተገኙበት ጥር 2 ቀን 2018 ዓ/ም ተቀምጧል።

Saint of the day

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300