በቅድስት መንበር የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ክፍል ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮጉጀሮቲ ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።

ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ክፍል (ዳይካስትሪ) ኃላፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጀሮቲ፣ ክቡር አባ ድሚትሮ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ክፍል ዋና ጸሃፊ፣ ክቡር አባ ጃሮዝላቭ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተወካይ ወደ ኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ገብተዋል።

ብፁዕነታቸው ወደኢትዮጵያ ሲገቡ በአዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት እና በቫቲካን ኤምባሲ በብፁዓን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ገዳማውያን እና የምዕመናን ተወካዮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በመቀጠልም በልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል በብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ካህናት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የጉብኝታቸውን ማስጀመሪያ የጸሎት መርሃግብር ተካሂዷል።

ጉብኝታቸውን በአዲስ አበባ ሀገረስብከት የሴቶች እድገት የሙያ ማሰልጠኛ እና በቅዱስ ዮሃንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የጀመሩ ሲሆን ተማሪዎችንም በስልጠና ላይ ሰላምታቸውን አቅርበዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በተቋሙ በመገኘትም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞችን አግኝተዋል። ብፁዕነታቸው በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ያለውን የሥራ ሂደት እና ዘርፈ ብዙ የአገልግሎት ዘርፎች ገለጻ ተደርጎላቸው አጠር ያለ ጉብኝት አድርገዋል። 


Leave a Reply

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300