በቅድስት መንበር የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ክፍል ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር ተገናኙ

በዛሬው ዕለት ለሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተገናኝተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ለቅዱስ ፓትሪያርኩ የርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ሌዎ 14ኛ መልዕክት ያቀረቡ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ እንግዶቹን በቢሯቸው በመቀበል በኢትዮጵያ ለሚኖራቸውም ቆይታ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ አባታዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል።

ብፁዓን ጳጳሳቱ በወቅታዊ የአለማችን ሰላም እና የክርስቲያኖች ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል። በተለይም በኢትዮጵያ እና በመላው አለም ክርስቲያኖች ላይ ለሚደርስ በደል በጸሎት ህብረት እና በጋራ የመስራት አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉብኝታቸውን በመቀጠል በአዲስ አበባ ሀገረስብከት የእማሆይ ተሬዛ ገዳም ቆይታ አድርገዋል። ስድስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ገዳም ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከገዳማውያት ጋር ታካሚዎችን እና በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።


Leave a Reply

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300