ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ የተላለፈ የኀዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በያዝነው ጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም. በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፣ መርቲና ሽርካ አካባቢ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የንጹሃን ሕይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን በታላቅ ሀዘን ሰምተናል።
ይህ ድርጊት በተደጋጋሚ በመፈጸሙ እጅግ ማዘኗን እየገለጸች የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መሰል ኢሰብዓዊነትን አጥብቃ ታወግዛለች። እንዲሁም በወለጋ እና በሞያሌ አካባቢዎች ተመሳሳይ የንጹሃን ግድያ በመፈጸሙ እጅግ ማዘናችንን እንገልጻለን።
ቤተክርስቲያናችን የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ መንግስት አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ ጥሪዋን ታቀርባለች።
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዚህ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ዘለዓለማዊ እረፍትን ያገኙ ዘንድ የጸሎት ጥሪዋን እያቀረበች የተሰማትን ሀዘን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ለተጎዱ ቤተሰቦች እየገለጸች ፈጣሪ እውነተኛ መጽናናት እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ
