ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ ታደሰ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት በ60ኛው መደበኛ ጉባኤያቸው ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ ታደሰን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት አድርገው ሾመዋል።

የጉባኤው ፕሬዝደንት በመሆን ሲያገለሉ የቆዪት የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የጡረታ እረፍትን ተከትሎ በተደረገው ምርጫ የአዲስ አበባ ሀገረስበከ‍ከት ሊቀጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴን ቀጣይ የጉባኤው ፕሬዝደንት አድርገው መርጠዋል። ብፁዕነታቸው ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎታቸውን እንደሚጀምሩም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ላለፉት 28 ዓመታት ጉባኤውን በፕሬዝደንትነት በመምራት ወደላቀ ከፍታ ላደረሱት ለብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የከበረ ምስጋናውን እያቀረበ አዲስ ለተሾሙት ፕሬዝደንት ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።


Leave a Reply

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300