ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጉ ዘንድ ግብዣ እና የጸሎት ጥሪ ቀረበ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ባሳለፍነው ሰኔ ወር በቅድስት መንበር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጋር ባደረጉት የካርዲናሎች ጉባኤ ለቅዱስነታቸው የግብዣ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በየአመቱ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚደረገው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞ የአፍሪካ ቀንድ ዋና ማዕከል ወደሆነችው ኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ እንደቀረበላቸው በመግለጽ ምዕመናን ለዚህ ምኞት መሳካት እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የዘመናት የታሪክ ባለቤት የሆነች፣ የአማኞች ሀገር፣ የአፍሪካ ማዕከል እና በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027 ለሚዘጋጀው 32ኛው የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) በአዘጋጅነት የተመረጠች ሀገር በመሆኗ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በቀጣይ ዓመት ለሚኖራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን ማካተት እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል።

ከሐምሌ 11-19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኬንያ ናይሮቢ በተካሔደው 21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤም ይህ ጥሪ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሌዎ 14ኛ መቅረቡ ተገልጿል።

ይህም ታላቅ እና የዘመናት የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ምኞት ምላሽ ይገኝ ዘንድ መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።


Leave a Reply

“በነፃ የተቀበላችሁት በነፃ ስጡ”

ማቴዎስ 10፡7-15

አስተንትኖ፡ የሚስዮናዊ ደቀመዝሙርነት ራስን መቻልን፣ መተማመንን እና ልግስናን ይጠይቃል። የተላክነው ለጥቅም ሳይሆን የምስራቹን ቃል ለማወጅና ለመባረክ ነው።

    The Catholic Bishops Conference of Ethiopia (CBCE)
  • Wawel Street, Besides of Catholic Cathedral, Piassa
  • CBCE@cbce-gs.org
  • scpr@eccsdco.org
  • +251-11-1550300